እኛ ምንድነን

ፍትሃዊ የስራ ማእከል  501c3  ትርፍ ኣልቦ ሁኖ ሰራተኞች ኣዲሱ የስያትል የስራ ህግ ለመፈለግ ቃል የገባ ማህበር
ነው።ስያትል ለከተማችን ድንቅ የሆኑ የስራ ህጎች ኣሳልፋለች፡ከነሱም ውስጥ በኣገር ደረጃ ከፍተኛ ሚኒማም ወጅ፡የኛ ተልእኮ እነዚህ የስራ መደበኛ ደንብ ለሁሉም ሰራተኛ እውን እንዲሆን ነው።

የምንሰራው ስራ

ፍትሃዊ የስራ ማእከል ለሰራተኞች የሚከተሉትን እርዳታ ይሰጣል

  • በተለያዩ ቃንቃዎች የሰራተኞች መብት የሚገልፅ እናቀርባለን
  • መብትህን እወቅ የሚል በተለያየ ቃንቃ ትምህርት (ስልጠና) እናደርጋለን
  • ሰራተኞች በነፃ የከተማ የስቴትና የፈደራል መንግስት መስሪያቤቶች  እንዲያገኙ እንረዳለን
  • በስራ ቦታ ሊኖር ስለሚችል ጥሰት ለሰራተኞች ነፃ ህጋዊ እርዳታ እንሰጣለን

የስያትል የስራ ህግ ጥያቄዎቻችህ መልስ ኣግኙ

በቅርብ ጊዜ በሁሉም ቃንቃዎች ፅሁፎች ይኖሩናል

በየዓመቱ ጃንዋሪ (ጥር) ወር የሲያትል ዝቅተኛው ደሞዝ ይጨምራል። ባሁኑ ጊዜ በትላልቅ ንግድ ሥራዎች የሠራተኞች ዝቅተኛው ደሞዝ $15.00 ነው፡ ($13.50 የሕክምና መድን ሽፋን የሚሰጡ ከሆን)፥ ለትናንሽ ንግድ ሥራዎች ሠራተኞች $11.00 ከ $2.00 ጉርሻ (ቲፕ) ጋር ወይም $13.።

ኣዲሱ የሚኒማም ወጅ ህግ ኣሰሪዎች በሚቀጥሉ ትንሽ ኣመታት በደርጃ ደሞዝ እንዲጨምሩ ያስችላቸዋል፡በ ጥር  2017 ሚኒማም ወጅ በትንሽ ይጨምራል፡ ግን የሰራተኞች ብዛትና የጤና ግልጋሎት ፕላን ማቅረብ መሰረት በማድረግ  ለሁሉ የሚከፈለው ደረጃ ይለያያል፡ ትናንሽ ስራዎች (500 ሰራተኞች ወይም ከዛ በታች) የሆኑ ወደ $15.00 ለመጨመር ረዘም ያለ ጊዜ ይወስድባቸዋል፡ትላልቅ ካምፓኒዎች ግን ጃኗሪ 1,2017 $15.00 ይደርሳል።

በሁለት ሳምንት ውስጥ በስያትል ውስጥ ለሁለት ሰዓት ከሰራህ ሚኒማም ወጅ ይከፈላል፡ በስራ ጊዜ በስያትል ከነዳህና  ለስራ ጉዳይ ካልቆምክ ላንተ ኣይመለከትም በስያትል መስራትህን ለማረጋገጥ ሪከርድ መያዝ ያስፈልጋል።

ከስያትል በስተቀር በሁሉም ዋሽንግቶን ሚኒማም ወጅ $9.47 ነው፡የፈደራል ሚኒማም ወጅ $7.25 ነው።

የፍትሃዊ የስራ ማእከል ሰራተኛ  በ 877 333 8898 ደውል፡እንደገና  ስያትል ኦፊስ ኦፍ ላቦር ስታንዳርድስ ወብ ሳይት ልትጎበኝ ትችላለህ።

ፒሴሴቲ የስያትል ሰራተኞች ራሳቸውም ሆነ ቤተሰባቸው ለማስታመም ሊከፈላቸው ይችላል።

ብያንስ ኣምስት ፉል ታይም ሰራተኞች ያሉበት የስራ ቦታ ሁሉ ፓይድ ሲክና ሴፍ ታይም ይገባቸዋል፡ ይህም ፉል ታይም ፓርት ታይምና ጊዜዊ ሰራተኞች ያጠቃልላል።

ኣምስት ወይም በላይ ሰራተኛ ያለበት ማንኛውም የስራ ቦታ ሙሉ ዓመት ፓይድ ሊቭ ያገኛሉ፡ፓይድ ሊቭ የሚገኘው በቀን ሳይሆን በሰዓት ነው።

ስራ ስትጀምር ፐይድ ሊቨ ማጠራቀም ትጀምራለህ፡በስራህ 180 ቀን (6 ወር) እስኪሞላህ ድረስ  ግን ፐይድ ሊቭ ለመጠቀም ኣትችልም።

ፐይድ ሊቭ ስትወስድ መደበኛ የስዓት ክፍያ ይከፈለሃል፡ከስያትል ሚኒማም ወጅ በታች ሊሆን ኣይችልም፡ በሲክ ሊቨ ጊዜ ኣሰሪዎች የጎደለ ቲፕና ኮሚሽን እንዲከፍሉ ኣይፈለግም።

በትንሽ ስራ (ስሞል ቢስነስ) የሚሰሩ ሰራተኞች ለያንዳንዱ ኣርባ ሰዓት  ኣንድ ሰዓት ፐይድ ሊቨ ያገኛሉ፡ወይም ኣንድ ሰዓት ለያንዳንድ ሳምንት፡ በትልቅ ካምፓን የሚሰሩ ለያንዳንዱ የ 30 ሰዓት ስራ ኣንድ ሰዓት የ ፐይድ ታይም ያገኛሉ፡ ለምሳሌ፡ 1 ኣንድ ሰዓት ለያንዳንዱ የ40 ሰዓት ይስራ ሳምንት፡ በ 52 ሳምንት በየዓመቱ (1×52=52/ 8 ሰዓት  በቀን)=6.5 ፒሴሴቲ ቀን በዓመት።

ለምሳሌ 1 ሰዓት ለያንዳንዱ 30 የስራ ሳምንት በ52 ሳምንት በዓመት ማለትፐይድ ሊቭ የሚሆነው 25% ፈጠን ብሎ  በትልቅ የስራ ቦታ ከትንሽ ሲወዳደር፡ፐይድ ሲክ ታይም ትልቅ የስራ ቦታ በግምት ወደ 8 ቀን በዓመት ይጨምራል።

ባል ወይም ሚስት (ዶመስቲክ ፓርትነር) ወላጆች ልጆች ኣያቶችና ማንኛው ብዝምድና ወይ በጋብቻ የተያያዘ ትልቅ ሰው በፒሴሴቲ ህግ መሰረት ቤተሰብ ይባላል።

በተከታታይ ከሶስት ቀን በላይ ፐይድ ሊቭ ለመውሰድ ከፈለክ  ኣሰሪዎችህ ተገቢ የሆነ ፅሁፍ ሊጠይቁ ይችላሉ ለዚህም የዶክተር ፅሁፍ በቂ ነው።

በፒኤስኤስቲ መሰረት ሴፍ ታይም  የሚያወራው ስለ ኣንድ ሰው ደህንነት ነው፡ ምሳሌ የቤት ብጥብጥ በፆታዊ ግኑኝነት ሰው መጉዳት ወይም ያለኣግባብ ሰው መከታተል ለራስህ ይሁን ቤተሰብ ወክለህ፡ ህጉ እንደገና ፐይድ ሊቭ ለህዝባዊ የጤና ወይም የኣስቸኩዋይ ነገር ያጠቃልላል ለምሳሌ በልጅ ትምህትቤት ኣንድ ነገር ቢፈጠር።

ኣሰሪዎች ተገቢ ፐይድ ሊቭ ለጠየቁ ሰራተኞች ሊቀጡ ወም ሊያባርሩ ኣይችሉም፡ወይም ፐይድ ሊቭ እንደ ያለፈቃድ ከስራ መቅረት ሊያስቡት ኣይችሉም፡ ሰራተኛ ግልፅ የሆነ ተደጋጋሚ ያላግባብነት ሲያሳይ(እንደ ለተወሰኑ ቀኖች ያለ ማስረጃ መቅረት ኣሰሪ ሊቀጣ ይችላል)

ስያትል ኦፊስ ኦፍ ሲቪል ራይት ማግኘት ትችላለህ ወይም ለእርዳታ ፍትሃዊ የስራ ማእከል 877 333 8898 መደወል ይቻላል።

የደሞዝ ስርቆት ወይም ወጅ ተፍት ማለት ኣሰሪ ሙሉ ወይም በከፊሉ ቸክ ሲይዝ ቲፕ ሰራተኛ ለሰራበት ሰዓትና መከፈል ለሚገባው ደሞዝ ያጠቃልላል።

ኣሰሪዎች ሰራተኛ ለሰራው ሰዓት መክፈል ኣለባቸው፡ቲፕና ሁሌም ቢያንስ ሚኒማም ወጅ ያጠቃልላል፡በተጨማሪ ኣሰሪዎች የደሞዝ ኣከፋፈል ሪፖርት ሪከርድ ቢያንስ ለሶስት ዓመት ማስቀመጥ ኣለባቸው፡ኣሰሪዎች በተጨማሪ ለእያንዳንዱ የደሞዝ ክፍያ ጊዜ የክፍያ ደረጃና የሚቀነስበት ለሰራተኞች በፅሁፍ ገለፃ ማቅረብ፡

ኣዎ፡ወጅ ተፍት (የደሞዝ ስርቆት) ኣቤቱታ እስከ ሶስት ዓመት ወደሁዋላ ሊሄድ ይችላል፡

ስያትል ኦፊስ ኦፍ ላቦር ስታንዳርድስ ያንተ ኣቤቱታ ይመረምራል፡ዋገ ተፍት መደረጉ ካገኙ ኣሰሪው የሁኣላ ያልተከፈለ ደሞዝ  ከወለድ፡ ከቅጣት ጋር እንዲከፍል ያዛል፡ኣንዳንድ ከባድ በሆኑ ጉዳዮች ኣሰሪው ተመርምሮ ሊታሰር ይችላል።

ፋይር ዎርክ ሰንተር(ፍትሃዊ የስራ ማእከል) በ 877 333 8898 ማግኘት ትችላለህ፡ ወይም የ ስያትል ኦፊስ ኦፍ ሌቦር ስታንዳርድስ ወብሳይት መጎብኘት ትችላለህ።

ባን ዘ ቦክስ የስያትል ኣሰሪዎች ስራ ኣመልካቾችን በወንጀል ጥፋተኛ ሁነው የተገኙ ስለመሆናቸው ወድያውኑ እንዳይጠይቁ የሚከለክል ህግ ነው፡ የወንጀል ረከርድ  ያላቸው ሰዎች የስራ እድል እንዲደርሳቸው ታሳቢ በማድረግ ነው፡ተደጋጋሚ ወንጀል እንዳይኖር ለመከላከል የረዳ መሆኑን ያረጋገጠ ነው።

ኣሰሪዎች በመጀመርያው ማመልከቻና ኢንተርቪይው ስለ ሰራተኞች የወንጀል ረከርድ  ለመጠየቅ ሳይፈቀድላቸውም፡መጀመርያ ይስራ ችሎታቸው ብቻ መርምረው ማስወጣት ከቻሉ በሁዋላ  እንደ መደበኛ ባክግራውንድ ሊጠይቁ ይችላሉ፡ለስራው ዝቅተኛው ተፈላጊነት የማታማላ ከሆንክ ኣሰሪ ከሌሎች ኣመልካቾች ውስጥ ሊያወጣህ ይችላል።

የወንጀል ሪኮርድ ካለህ ኣሰሪው ኣንተን ከሌሎች ብቁ ከሆኑ ኣመልካቾች ከማውጣቱ በፊት የሪኮርዱ  ሁኔታ ለመግለፅ ወይም ለማስረዳት መብት ኣለህ።

ለእርዳታ ፍትሃዊ ዎርክ ሰንተር(ፍትሃዊ የስራ ማእከል) 877 333 8898 መደወል ትችላለህ፡እንደገና ስያትል ኦፊስ ኦፍ ሌቦር ስታንዳርድስ ማግኘት ይቻላል።